ዳኛቸው ወርቁ
Biography
1. In English
Dagnachew Worku’s Biography by Molvaer
Dagnachew Worku by Sibhat G Egziabher
ውይይት – ያማርኛ ልቦለድ እድገት ከ‹‹ጦቢያ›› እስከ ‹‹አደፍርስ››
በዳኛቸው ወርቁ አደፍርስ ውስጥ የሚታዩ ሳይንሳዊ አገላለፆች ሂሳዊ ምልከታ – ኤፍሬም አሰፋ ጨቦ
Adefris- A Novel
አጭር ልቦለዶች ዝርዝር
- አለቀ በቃ
- ምን ይሳነዋል
- አረፈ
በ “አደፍርስ” ልቦለድ ውስጥ ደራሲው ዳኛቸው ወርቁ ልቡሰ ጥላው አነሳስቶት የገቡ ምሳሌያዊ አነጋገሮች፡
ዝንብ ቢጠራቀም ቋጫ አይከፍትም
ዝናብ ባይመጣ ሁሉ ቤት እንግዳ ባይመጣ ሁሉ ሴት
የወደዱትን ቢያጡ የጠሉትን ይቀላውጡ
ጠጉራም ውሻ አለ ሱሉት በራብ ይሞት
አውራ ዶሮ በየፍጉ ክምር ላይ ቆሞ ይጮሃል
ፍላፃ ባየር ውስጥ አልፎ ፍለጋ አይተውም
ለቀንዳም በሬ ቤት አትከልክለው ቀንዱ ይከለክለዋል
ሰኔና ሰኞ
በሰም የተጣበቀ ጥርስ ቢስቁበት አይደምቅ ቢበሉበት አያደቅ
ሰው ሆኖ የማይብስ እንጨት ሆኖ የማይጨስ
ሰው ከስሕተት ብረት ከዝገት
ብረት ካልፈላ አይላላ
ደም ማልቀስ ድንጋይ መንከስ
ወረቱን እንደተቀማ ነጋዴ ዋግ እንደመታው ስንዴ
ከዝንጀሮ ጋሜ ያንበሳ መላጣ
ተስካር ያየ ተማሪ ሸቀጥ ያየ አጣሪ
እህል ያለው ፈርዛዛ ገንዘብ ያለው ቀበዝባዛ
ወዶ የዋጡት ቅልጥም ከፍርምባ ይጥም
ወስፌ ቢለግም ቅቤ አይወጋም
መዘዘኛ ላም የሰው ልጅ አስከትላ ነበር
ጅብ ከሄደ ውሻ ጮኸ
የዛሬ ልጆች እዩኝ እዩኝ ድብቁኝ ደብቁኝ ለማለት ነው ኋላ
በእውር ጎዳና ብርቅ ነው አንድ አይና
ያላዋቂ ሳሚ ንፍጥ ይለቀልቃል
ሰው እንደቤቱ እንጂ እንደጎረቤቱ አይበላም
የፈሰሰ ውሀ አይታፈስም
ሲሮጡ የታጠቁት ሲሮጡ ይፈታል