የሕይወት ታሪኩ በአጭሩ
ስመጥርና ሁለት ዓይና (ደራሲና ጋዜጠኛ) የነበረው በዓሉ ግርማ ቅዳሜ መስከረም 12 ቀን 1932 ዓ.ም. በኢሉባቦር ጠቅላይ ግዛት፣ ሱጴ ከሕንዳዊው አባቱ ባቡና ኢትዮጵያዊት እናቱ መወለዱ ይታወቃል፡፡
በዓሉ፣ በሱጴ የቄስ ትምህርት ቤትን በሕፃንነቱ ከተከታተለ በኋላ በ10 ዓመቱ አዲስ አበባ በመምጣት በልዕልት ዘነበ ወርቅ አዳሪ ትምህርት ቤት የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርቱን ተከታትሏል፡፡ ቀለም የገባው ትጉህና ብሩኅ ተማሪ በመሆኑ በጄኔራል ዊንጌት ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ስኮላርሺፕ በማግኘት ትምህርቱን ለማጠናቀቅ ችሏል፡፡ የጋዜጠኝነትና የፈጠራ ጽሑፍ ደራሲነት ጥሪውን የተቀበለውም ከዚያው ነው፡፡
በ1954 ዓ.ም. የመጀመሪያ ዲግሪውን በፖለቲካል ሳይንስና ጆርናሊዝም ከቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ያገኘው በዓሉ፣ ከትምህርቱ በተጓዳኝ ለኢትዮጵያን ሔራልድ ጋዜጣ፣ እንዲሁም በዩኒቨርሲቲው ጋዜጣ “ኒውስ ኤንድ ቪው” ዋና አዘጋጅ ሆኖ ሰርቷል፡፡
በተመሳሳይ ትምህርት ሁለተኛ ዲግሪውን አሁን ፋውንዴሽኑ በተመሰረተበት ሚችጋን ስቴት ዩኒቨርሲቲ አግኝቷል፡፡
በጋዜጠኛነቱ ቅድመ አብዮት የመነን መጽሔት፣ የአዲስ ሪፖርተር፣ አዲስ ዘመን ዋና አዘጋጅ የነበረው በዓሉ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ኃላፊ፣ በ1969 ዓ.ም. የማስታወቂያና መርሐ ብሔር ሚኒስቴር ቋሚ ተጠሪ (ሚኒስትር ዴኤታ) ነበር፡፡
“የኪነት ሰዎች ዓላማና ግብ ሐቅ ነው” በሚለውና በልብ ወለዶቹም ባንፀባረቀው መርሑ የሚታወቀው በዓሉ፣ በሕልውና ዘመኑ ስድስት ረዥም ልብ ወለዶቹን ለንባብ አብቅቷል፡፡
ዘመናዊ የአማርኛ ልብ ወለድ ታሪክ ውስጥ ከፋና ወጊዎቹ ተርታ ያሳለፉት የመጀመሪያው ድርሰቱ “ከአድማስ ባሻገር” (1962) ሲሆን ተከታዩ “የሕሊና ደወል” (1966) ነው፡፡
የሰውን ሕይወት ጠልቆ የሚያይበት፣ በኪናዊ አፃፃፉ ስኬት ያገኘበት እንደሆነ ይነገርለታል፡፡ አንድ ሐያሲም የሰውን ሕይወት ዘይቤና ገበና ገልጾ በማሳየት ረገድ ከፈረንሳዊው ደራሲ ባልዛክ ጋር አነፃፅሮታል፡፡
በድኅረ አብዮት፣ የመረጋጋት ዘመን ሲመጣ፣ ቆሞ የነበረው የድርሰት ጉዞ የባተው በዓሉ በ1972 ዓ.ም. ባወጣው “የቀይ ኮከብ ጥሪ” ልብ ወለዱ ነበር፡፡ በማስከተልም “ደራሲው” (1972) እና “ሀዲስ” (1975) በመጨረሻም በ1975 “ኦሮማይ”ን ለንባብ አብቅቷል፡፡
ለደራሲው መሰወር ምክንያት ከሆነው “ኦሮማይ” በፊትና ከ”ሀዲስ” በኋላ ብቸኛው የአጭር ልብ ወለድ ሥራው በየካቲት መጽሔት፣ የካቲት ወር 1975 ዓ.ም. እትም “የፍጻሜው መጀመሪያ” በሚል ርእስ አውጥቶ ነበር፡፡
“ጽሑፍ ሕይወቴ ነው፡፡ ከዚያ ውጪ ሌላ የሕይወት ምኞት የለኝም፡፡ ነፍሴ ራስዋን ለመግለጽ የምታደርገውን ጥረት መቀጠል አለባት፡፡ አንድ ቀን ምናልባት አንድ ቀን ራስዋን ለመግለጽ ትችል ይሆናል” ያለው በዓሉ ግርማ፣ በተወለደባት የዕረፍት ቀን ቅዳሜ፣ በተሰወረባት ዕለተ ቅዳሜ ይፋ የሆነው ፋውንዴሽን፣ ነፍሱንና ሕይወቱን ለሥነ ጽሑፍና ለጋዜጠኞች ትውልድ ያበረከተውን በረከት ይገልጽለት ይሆናል፡፡
የበዓሉ ግርማ ድርሰቶች በዩኒቨርሲቲዎችና በዓለም አቀፍ ጉባኤዎች የጥናት ርእሶች ለመሆን በቅተዋል፡፡ ከመጀመሪያ ዲግሪ እስከ ዱክትርና ድረስ መመረቂያ ጽሑፍ የሠሩ የጥናት ጽሑፍም ያቀረቡ በርካቶች ናቸው፡፡ ከእነዚህም መካከል በ1995 ዓ.ም. በኒውዮርክ በተካሄደው የአፍሪካ ሥነ ጽሑፍ ጉባኤ የጥናት ርእስ ሆኖ በጸጋዬ ወዳጆ የቀረበው አንዱ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ደራስያን ችግሮች በበዓሉ ግርማ ልብ ወለዶች መስኮትነት (The Novels of Baalu Girma: A Window in to the Ethiopian Writer’s Problems) በሚል ጭብጥ ዙርያ ያተኮረ ነው፡፡ የቅርቡ ደግሞ በ1999 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለሁለተኛ ዲግሪ ማሟያ ጥናቱን የሠራው ኤልያስ አያልነህ፣ “ገፀ ክርስቶስ በበዓሉ ግርማ ቅድመ አብዮት ኖቭሎች” በሚል ርእስ ለየት ያለ ዳሰሳ አቅርቦበታል፡፡
In English
Biography of Baalu Girma
Related works
የበአሉ ግርማ ጠንካራ የሴት ገጸ ባህርያት-ዘሪሁን አስፋው
የበአሉ ግርማ ስራዎች በአበራ ለማ እይታ
Baalu Girma’s works coming soon.
በአሉ ከሀገራችን ደራሲዎች ከታላላቆቹ አንዱ የነበረ ሰው ነበረ ። ነገር ግን ህይወቱ በማይታቅ ሁኔታ ማለፉ አሳዛኝ ቢሆንም ስራው ግን ታላቅ መሆኑ የታወቀ ነው ።
bealu bememegetu des bilonal
የበዓሉ ግርማ ስራዎች ትወልድ በትልቀት ሊመረምራቸዉ ይገባል እንደ ሻማ ቀል_ የሞተ ድንቅ ደራሲ ነዉ
በዓሉ ግርማን የማውቀው በ ኦሮማይ እና ሀዲስ ስራዎቹ ነው
እጅግ ምጡቅ እና የተዋበ ሀሳብን እንባቢን አርክቶ የማስተላለፍ ብቃት አለው ስራዎቹ ከመቃብር በላይ እድርገውት ዛሬም ይነበባል ይደነቃል ይወደሳል ጀግና ህያው ነው
በፁህፍፎቹ ብዙ ግንዛቤን አግቼበታለው
መድሐኒአለም በገነት ያኑርህ
Can you tell me the author that wrote about Bealu Girma with their book names
betame ymeyasazine nw sela balu asazagne marage y samute magabite 7,2015 ec b fm addise 97 ly nw……