ትርጉም በመምህር ሀይለ ማርያም ላቀው
መጽሐፈ ምስጢር በ13ኛው መቶ ክፍለ ዘመን በአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ የተደረሰ በሀይማኖቱ ጥልቅ ምስጢራትን፣ በተጠያቃዊ /Logical/ መንገድ በአመክንዩ ተመስርቶ ክርራዊ አቀራረቦችን የያዘ ታላቅ የጥበብ፣ የታሪክ፣ እና የፍልስፍና መድብል ሃይማኖታዊ መጽሐፍ ነው፡፡ በውስጡ የያዘውን ምስጢርና ቁምነገር ስመለከተው፤ የጥናትና ምርምር ስራ በሀገራችን ባላደገበት በዚያ ዘመን አንደ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ያሉ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሊቃውንት ምን ያህል በምርምር ሥራ ቀድመው ሄደው እንደነበር የሚያብራራና የሚያረጋግጥ ነው፡፡ ይህንን ድንቅ ስራ መምህር ኀይለማርያም ላቀው ከቤተ ክርስቲያኑ ያገኘውን ዕውቀትና ልምድ፣ ከአባቶቹም ያገኘውን ምክር በመጠቀም ተርጉሞ ለንባብ አብቅቷል፡፡ ይህ ስራ እንደዚህ ያሉና ዕፁብ ድንቅ የሆኑ ሳይተረጉሙና ሳይታተሙ በየገዳማቱና በየአድባራቱ የተቀመጡበትን በዕውቀትና በጥበብ የበለፀጉ ሌሎች ስራዎችንም ተርጉሞ ለንባብ ለማብቃት ብዙ ምሁራን ይጋብዛል ብዬ አስባለሁ፡፡…
ከመፅሐፉ ሽፋን የተወሰደ
የአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ገድል ቀጥሎ ቀርቧል
10 Responses to አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ