የሕይወት ታሪኩ በአጭሩ

ስመጥርና ሁለት ዓይና (ደራሲና ጋዜጠኛ) የነበረው በዓሉ ግርማ ቅዳሜ መስከረም 12 ቀን 1932 ዓ.ም. በኢሉባቦር ጠቅላይ ግዛት፣ ሱጴ ከሕንዳዊው አባቱ ባቡና ኢትዮጵያዊት እናቱ መወለዱ ይታወቃል፡፡  በዓሉ፣ በሱጴ የቄስ ትምህርት ቤትን በሕፃንነቱ ከተከታተለ በኋላ በ10 ዓመቱ አዲስ አበባ በመምጣት በልዕልት ዘነበ ወርቅ አዳሪ ትምህርት ቤት የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርቱን ተከታትሏል፡፡ ቀለም የገባው ትጉህና ብሩኅ ተማሪ በመሆኑ በጄኔራል ዊንጌት ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ስኮላርሺፕ በማግኘት ትምህርቱን ለማጠናቀቅ ችሏል፡፡ የጋዜጠኝነትና የፈጠራ ጽሑፍ ደራሲነት ጥሪውን የተቀበለውም ከዚያው ነው፡፡  በ1954 ዓ.ም. የመጀመሪያ ዲግሪውን በፖለቲካል ሳይንስና ጆርናሊዝም ከቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ያገኘው በዓሉ፣ ከትምህርቱ በተጓዳኝ ለኢትዮጵያን ሔራልድ ጋዜጣ፣ እንዲሁም በዩኒቨርሲቲው ጋዜጣ “ኒውስ ኤንድ ቪው” ዋና አዘጋጅ ሆኖ ሰርቷል፡፡

ስለ በአሉ ግርማ የበለጠ ለመንበብ እንዲሁም ስራዎቹን ለመመልከት ከፈለጉ ይሁን ይጫኑ፡፡ በአሉ ግርማ